- Sun, 10/07/2012 - 11:46
- 0 Comments
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ከኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚነት ተነስተው በተራ አባልነት እንዲቀጥሉ ድርጅቱ መወሰኑን ምንጮች ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡
የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ከመስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ዓመታዊ ጉባዔው ላይ፣ በሟች እናታቸው መኖሪያ ላይ እያሠሩት ካለው መስጅድ ጋር በተያያዘ የተገመገሙት ሚኒስትር ጁነዲን፣ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈጸማቸውንና ካሉበት ኃላፊነትና ሥልጣን አኳያ ተገቢ ያልሆነ ሥራ መሥራታቸው በዋናነት እንደተገመገሙበት ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ጁነዲን በእናታቸው የኑዛዜ ቃል መሠረት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ መስጅድ ለማስገንባት፣ በሚኒስትርነታቸው ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ለመስጅዱ ማስጨረሻ ከሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ ዕርዳታ በመጠየቃቸው፣ የመስጅዱ የመጀመሪያ ደረጃ ምርቃት ሲደረግ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ተገኝተው 500 ቅዱስ ቁርአንና 50 ሺሕ ብር ዕርዳታ መስጠታቸውን ራሳቸው አቶ ጁነዲን በጻፉት ደብዳቤ አረጋግጠዋል፡፡
ባለቤታቸው አምባሳደሩ የሰጡትን 50 ሺሕ ብር ለመቀበል ኤምባሲ ሄደው ተቀብለው ሲወጡ፣ ለሽብር ተግባር የሚውል ገንዘብ ተቀብለዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ አቶ ጁነዲን በጻፉት ደብዳቤ ግን ባለቤታቸው የተከበሩ የቤት እመቤት መሆናቸውን ገልጸው ነበር፡፡
Read the complete story from The Reporter
- 127 reads
Post new comment