- Wed, 08/29/2012 - 00:30
- 0 Comments
በዊኒፔግ ከተማ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
እንደሚታወቀው በተለያዩ የአለም ክፍላት ያሉ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሕልፈት የደረሰባቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ፡፡
እኛ በዊኒፔግ ከተማ የምንገኝ ኢትዮጵያውያንም ሐዘናችንን ለጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ቤተሰብ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለመግለጽ የሚያስችል አጭር መድረክ አዘጋጅተናል፡፡
ከ ታላቅ አክብሮት ጋር፡፡
---
To Ethiopians and friends of Ethiopia in Winnipeg and surrounding areas
Ethiopians from all walks of life, friends of Ethiopia and the international community all over the world have been mourning the sudden death of PM Meles Zenawi.
In this regard we Ethiopian who reside in Winnipeg have organized a memorial service to express our deepest condolences to the family of PM Meles and the Ethiopian people. So please join us:
Place: 129 Dagmar Street
South Sudan Community Center)
Date : Saturday September 1, 2012 @ 5 Pm
For further information call (204)-390-7135
Thank you
የሐዘን መግለጫ
የክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ከተሰማ እነሆ ስምነት ቀናት ተቆጠሩ፣ እጅግ ከባድ የሆኑ ስምንት የሃዘን ቀናት፡፡ እኛ በዊኒፔግ ከተማ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን፣ ምንም እንኳን በአገራችን ሆነን ሃዘናችንን ከወገናችን ጋር ለመካፈል ባንታደልም፣ ካለንበት ሆነን የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን ለመግለፅ እነሆ ዛሬ መሰባሰብ ቻልን፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ፣ ሕዝባቸውን ከነበረው ጨቋኝ አገዛዝ ለመታደግ ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይከታተሉት የነበረውን የሕክምና ትምህርታቸውን ካቋረጡበት ጊዜ ጀምሮ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እድሜያቸውን በሙሉ አገራቸውን እና ሕዝባቸውን ሲያገለግሉ የኖሩ ታላቅ መሪ ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ፣ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን በተለያዩ የአለም መድረኮች ላይ በፍፁም ብቃት መወከል የቻሉ፤ በተግባርም ታሪካዊ እምርታ ያሳዩ በሳል መሪ ነበሩ፡፡
ያለመታደል ሆነና ድካም የማያውቁት ይህ ታላቅ መሪ ድንገት ዛሬ ደከሙ፡፡
ሽንፈት የማያውቁት እኝህ ጀግና ዛሬ በሞት ተሸነፉ፡፡
እረፍት እንደናፈቃቸው ወደ ዘልአለማዊው እረፍት ሄዱ፡፡
እግዚአብሔር ነብሳቸውን በገነት ያኖር ዘነድ ፤ ለቤተሰባቸው እና በሐዘን ልቡ ለተሰበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይሰጥ ዘንድ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን፡፡
ፈጣሪ አገራችንን ይባርክ፡፡ የተጀመሩት የልማት ስራዎች ፍጻሜ ላይ እንዲደርሱ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንድናደርግ ይርዳን ፡፡ አሜን፡፡
- 225 reads
Post new comment